በፕሬስ ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች፤ በ2013/14 ከሁሉም በላይ ጋዜጠኞችን የገደሉ ሀገሮች
በጄኒፈር ደንሃም/ሲፒጄ ምክትል ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር ጥር 5፣ 2014 የታተመ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲፒጄ) በዓመቱ በሰበሰበው አጠቃላይ መረጃ፣ በ2013/14 ቢያንስ 27 ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ መገደላቸውን እና ህንድ እና ሜክሲኮም ብዙ የሚዲያ ሰራተኞች ከተገደሉባቸው ሀገራት መካክል ቀዳሚ መሆናቸውን አስታውቋል። በፕሬስ ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ያካተተው የሲፒጄ ሪፖርት ከታተመ ከህዳር 30፣ 2014 ወዲህ፣ የተገደሉት የጋዜጠኞች ቁጥር በሦስት…
በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስር ቤት የታጎሩ ጋዜጠኞች ቁጥር ጨምሯል
በዓለም ላይ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር በ2013/14 ሌላ አዲስ “ክብረ-ወሰን” አስመዝግቧል። አዲስ የቴክኖሎጂ እና የደህንነት ህጎችን በመጥቀስ፣ከእስያ እስከ አውሮፓ እስከ አፍሪካ ያሉ አፋኝ መንግስታት በነጻው ፕሬስ ላይ አስከፊ እርምጃ ወስደዋል። በኤዲቶሪያል ዳይሬክተር አርለን ጌትስ የቀረበ የሲፒጄ ልዩ ዘገባ። ህዳር 30፣ 2014 የታተመ ኒው ዮርክ ይህ ዓመት ለፕሬስ ነፃነት ተሟጋቾች በተለየ ሁኔታ በጣም አስከፊ ጊዜ ነበር። በ2013/14…
በዓለም ዙሪያ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል
ቻይና በዓለም ላይ እጅግ አስከፊ ጋዘጠኞችን አሳሪ በመሆን ቀጥላለች፤ ህንድ እና ሜክሲኮ አስቃቂ አሳሪ ከሚባሉት ሀገሮች ከመጀመሪያዎቹ ተርታ ተሰልፈዋል። ኒውዮርክ ህዳር 30 2014— በ2013/14 እስር ቤት ውስጥ የታጎሩ የጋዜጠኞች ቁጥር አዲስ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል፤ 293 ጋዜጠኞች ለእስር የተዳረጉበት ይህ ዓመት፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በሚዲያ ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች በዓለም ዙሪያ እየተስፋፋ በመጣ ቁጥር፣ ገለልተኛ ዘገባዎችን…
የኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነት በአንድ ወቅት ከፍተኛ ተስፋ ፈንጥቆበት የነበረውን የፕሬስ ነፃነት ደብዛውን አጠፋው
በሙቶኪ ሙሞ አውሎ ሚዲያ ሴንተር የተሰኘው የኢትዮጵያ ኦንላይን የዜና አውታር የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን አስተዳደር በመተቸቱ ከመንግስት በሚደርስበት “ጫና እና መሰናክል” የተነሳ ድርጅቱን ዘግቶ ሰራተኞቹን በሙሉ ለማሰናበት መገደዱን በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በፌስቡክ ገፁ ባሰፈረው ልጥፍ አስታውቋል። የሚዲያ ሪፖርትስ እና የሲፒጄ ዘገባ እንደሚያስረዳው፣ ድርጅቱ የተዘጋው፣ በሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ በርካታ የአውሎ ሚዲያ ሴንተር ጋዜጠኞች እና…
ዲጅታል ደህንነት፤ የኢንተርኔት መዘጋት
የኢንተርኔት መዘጋት ለፕሬስ ነፃነት ከባድ መዘዝ እንዳለው እና ጋዜጠኞችንም ስራቸውን በብቃት ለማከናዎን አዳጋች እያደረገባቸው እደሆነ ሲፒጄ አረጋግጧል። ኢንተርኔት ተዘጋ ወይም ተገደበ ማለት፣ የሚዲያ ሰራተኞች አንድ ሁነት እስኪፈጠር ድረስ ምንጮችን ማግኘት፣ የመረጃን እውነታ ፍተሻ ማድረግ ወይም ታሪኮችን መሰነድ አይችሉም ማለት ነው። ኢንተርኔት ሊዘጋ የሚችለው ባብዛኛው በግጭት፣ በፖለቲካ አለመረጋጋት ወይም በምርጫ ወቅቶች ሲሆን፣ እንደ አክሰስ ናው (Access…
የ2013 የኢትዮጲያ ምርጫ፤ የጋዜጠኞች የደህንነት ኪት
በመላው ሀገሪቱ ውጥረት በነገሰበት ሁኔታ፣ በመጭው ሰኔ አጋማሽ አጠቃላይ ምርጫ ለማካሄድ፣ ኢትዮጵያ ቀን ቆርጣለች። በትግራይ ውስጥ በህዳር ወር የተከሰተው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው። የሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ በሌሎች በርካታ ክልሎችም፣ በብሔሮችና ጎሳዎች መካካል በሚፈጠር ግጭት እና በተቃውሞዎች የተነሳ፣ መጠነ-ሰፊ ነውጦች እና ዘግናኝ አደጋዎች ታይተዋል። የሲፒ ጥናት እንደሚያሳየው፣ ከህዳር 22፣ 2013 ጀምሮ፣ ቢያንስ ሰባት የሚሆኑ ጋዜጠኞች ዘብጥያ…
ምርጫን የተመለከተ የተሳሳተ መረጃ በዓለም ዙሪያ እየተከሰተ ነው፤ እነዚህ ጋዜጠኞች ደግሞ እየተፋለሙት ነው
በሪቤካ ሬድሌሞር/የሲ.ፒ.ጄ ኦዲየንስ ኢንጌጅመንት አስተባባሪ ታህሳስ 28 ቀን 2013 ላይ በተደረገው የካፒቶል የዓመጽ ሰልፍ ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ ባለበት ሁኔታም፣ አሁን ድረስ ስለ አሜሪካ ምርጫ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ አሳሳቢነት እንደቀጠለ ነው፡፡ ይህን አይነት ክስተት እየተጋፈጠች ያለቸው ግን አሜሪካ ብቻ አይደለችም፡፡ በተለይ እንደ ብሄራዊ ምርጫ ካሉ ታላላቅ ሁነቶች ጋር በተያያዘ የሀሰትኛ መረጃ ስርጭት በዓለም ዙሪያ እየተከሰተ ነው፡፡ የበዝፊድ ኒውስ…
የዲጂታል ደህንነት ኪት
የዲጂታል ደህንነት ኪት በመጨረሻ የተሻሻለው፣ ሚያዚያ 13 2013 ዓ.ም ጋዜጠኞች የወቅቱን የዲጂታል ደህንነት ዜናዎችን እና እንደ ምንተፋ (hacking)፣ ፊሺንግ (phishing) እና ክትትልን (surveillance) ባሉ ስጋቶች ላይ የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎችን በመከታተል ራሳቸውንና የመረጃ ምንጮቻቸውን መከላከል አለባቸው፡፡ ጋዜጠኞች ሃላፊነት ሰለወስዱበት መረጃና መረጃው ባልተገባ ሰው እጅ ቢገባ ምን ሊፈጠር እንደሚችል በማሰብ አካውንቶቻቸውን፣ መሣሪያዎቻቸውን፣ ግንኙነቶቻቸውን እና የመስመር ላይ እንቅስቃሴዎቻቸውን…
የዲጂታል ደህንነት፤ የታለሙ የመስመር ላይ ጥቃቶችን መከላከል
መስከረም 18 ቀን፣ 2013 የተሻሻለ በተሳሳተ መረጃ፣ በሴራ ንድፈ ሀሳቦች ወይም በሀሰተኛ ዜናዎች ላይ ሪፖርት የሚያደርጉ ጋዜጠኞች እነዚህን አመለካከቶች በሚያመነጩ ወይም በሚደግፉ፣ ወይም ደግሞ ጠንካራ የፖለቲካ ዝንባሌ ባላቸው ሰዎች አማካኝነት የመረብ ላይ ጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ። የዚህ ዓይነቱን መረጃ በመስመር ላይ ማሰራጨትን የሚደግፉ ሰዎች፣ ጋዜጠኞችን ከመስመር ላይ ግንኙነት ለማስወጣት እና ተአማኒነታቸውን ለማጉደፍ የተቀናጁ ጥቃቶችን ሊያደራጁ ይችላሉ።…
የአካል እና ዲጂታል ደህንነት – እስር እና በእስር መቆየት
የፈላጭ ቆራጭ አገዛዞች ወይም ሀይለኛ ወታደራዊ እና የፖሊስ አስተዳድር ባሉባቸው ሀገራት በመሄድ እንደ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ እንደ ሙስና ወይም የእርስ በእርስ ግጭቶች ያሉ የዜና ስራዎችን በሚዘግቡብት ወቅት፣ ለእስራት ሊጋለጡ ይችላሉ። እንዲህ ባላ ጊዜ፣ ከባለሥልጣናቱ ዘንድ ተቃዎሞ ሲያጋጥመዎ፣ ተቃዎሞው ሕጋዊ ባይሆንም እንኳ ለደህንነትዎ ሲባል፣ እነርሱ የሚሉዎትን መስማት ብልህነት ነው፡፡ ደህንነታቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ ይችሉ ዘንድ፣ ጋዜጠኞች…